ደንቦች እና ሁኔታዎች
ደንቦች እና ሁኔታዎች
1. መግቢያ
1.1. መነሻ ደንቦች
- 1.1.1.ኩባንያው መርኬ ቤትንግ የንግድ ስያሜው ሻምፕዮን ቤት በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ተመዝግቦ አድራሻው አዲስ አበባ ኢትዮጵያ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 08 አማጋይ ህንጻ ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኝ የኩባንያው ግ.ከ.መ.ቁ 0067205939 በስፖርት ውርርድ ፈቃድ የተሰጠው እና ይህም አግባብነት ባለው የስፖርት ውርርድ መምሪያ ቁጥር 83/2005፣ መሰረት የንግድ ፈቃድ ቁጥር 054/2012 ( ከዚህ በኋላ ኩባንያ ተብሎ የሚጠራ) ህጋዊ ፈቃድ ተሰጥቶት የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በአጠቃላይ በመረጃ መረብ www.championbet.et (ከዚህ በኋላ የኢንተርኔት የስፖርት ይወራረዱ ያሸንፉ) የስፖርት ይወራረዱ ያሸንፉ ስራዎች ላይ ለመሰማራት የተመዘገበ እና ህጋዊ ፈቃድ የተሰጠው የንግድ ድርጅት ነው፡፡
- 1.1.2. ይህ የስፖርት ይወራረዱ ያሸንፉ የስራ እንቅስቃሴ ህጎች እና ደንቦች በደንበኛው እና በድርጅቱ መካከል የተፈረሙ ወይም የተፈጸሙ የውል ስምምነቶች አካል በመሆን በሁለቱም ላይ ተፈጻሚነት ያላቸው የስምምነት ህጎች እና ደንቦች ናቸው፡፡ በዚህ መሰረት የስምምነት ህጎቹ እና ደንቦቹን በአግባቡ ተግባራዊ ያለማድረግ የይወራረዱ ያሸንፉ ስራ ተቀባይነት የሚያሳጣ ይሆናል፡፡
- 1.2 የስምምነት ህጎቹ ትርጓሜዎች
- 1.2.1. ደንበኛ- ማለት ማንኛውም በዚህ የስፖርት ውድድር ይወራረዱ ያሸንፉ ስራ እንቅስቃሴ ውስጥ በቀጥታ የመሳተፍ እና እድሜው ከ21 አመት በላይ የሆነ ግለሰብ ማለት ነው፡፡
- 1.2.2. የስፖርት ውድድር ይወራረዱ ያሸንፉ- ማለት በእነዚህ የስምምነት ህጎች እና ደንቦች ተፈጻሚነት አላማ ሲባል የስፖርት ውድድር ይወራረዱ ያሸንፉ ማለት በይወራረዱ ያሸንፉ ጽ/ቤት ተገኝተው ለውርርዱ ትኬት ገዝተው የሚወራረድ ማንኛውም ደንበኛ ማለት ነው፡፡ የስፖርት ይወራረዱ ያሸንፉ ትኬትም ይህንኑ ለማስተናገድ በተቀመጡ ሰራተኞች አማካኝነትበጽ/ቤቱ የሚስተናገድ ይሆናል፡፡ የስፖርት ውድድር ይወራረዱ ያሸንፉ የውድድር አይነት በስፖርት ውድድር ወቅት አሸናፊው አስቀድሞ በመገመት ወይም አሸናፊ አስቀድሞ ከመገመት ጋር ተያይዞ የማሸነፍ ውድድር ወይም ጨዋታ ማለት ሲሆን ይህም በትክክለኛው በህዝባዊ እውነታ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ ትክክለኛ የስፖርት ውድድር ውጤት በትክክል በመገመት የሚተገበር ይሆናል፡፡ ማሸነፍ ወይም መሸነፍ በእድል ላይ የተመሰረተ ሲሆን ይህም ቀደም ብሎ ባልተለመደ አሰራር ስርአት እና ድርጊቶች ዌም ዝግጅቶች በተለይ ከሚከመናወኑ ስፖርት ወድድሮቭ ጋር ተያይዞ ወይም ሌሎች ከህዝባዊ ፍላጎት ጋርተያይዞ የሚደረገው ትክክለኛ ግምት ላይ የተመሰረተ የመወራረድ እና የማሸነፍ ወይም የመሸነፍ ሂደት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ አስፈላጊ በሆነው ግምት ላሸነፈው አካል በህዝባዊ ፍላጎት አኳኋን ወይም ህዝባዊ ፍላጎትን ባልተጻረረ አሰራር አሸናፊው ወይም ተሸናፊው የሚገለጽ እና የሚታወቅ ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜም በትክክለኛ መንገድ ግምቱን በማስመዝገብ ያሸነፈው አካል በቀጥታ የሚፈጽመው ክፍያ ቀደም ብሎ ሲወራረድ በገመተው የማሸነፍ ኦዶች ጋት ተያይዞ የሚፈጸም እና የሚከፈል ይሆናል፡፡ በስፖርት ውድድር ይወራረዱ ያሸንፉ ሂደቶች ተቀባይነት የሚኖራቸው አጫዋቹ ድርጅት በሰጠው የአሸናፊነት ኦድ/ግምት መሰረት ብቻ የሚፈጸም ይሆናል፡፡ የማንኛውም የስፖርት ውድድር ይወራረዱ ያሸንፉ የአሸናፊነት ኦድ/ግምት በድርጅቱ በተሰጠው የውርርድ ኦድ/ግምት መሰረት ተመሳሳይ በሆነ አካሄድ የሚፈጸም ሲሆን የይወራረዱ ያሸንፉ ጊዜ ተቀባይነት ያለው አሰራር መሰረት አድርጎ ድርጅቱ የማሸነፍ ኦዶች/ግምቶችን አግባብነት ባለው ህጉና ደንቡ መሰረት የመቀየር መብቱ የተጠበቀ ሲሆን በዚህ አሰራር መሰረትም የታተሙ ወይም የተዘጋጁ የማሸነፍ ኦዶች/ግምቶች ሁሉ የግድ ትክክል ናቸው ማለት አይድለም፡፡
- 1.2.3. መደብ ማለት ደንበኛው በሚወራረድብት ጊዜ የሚከፍለው ወይም ከፍሎ ትኬት የሚወስደው ማለት ነው፡፡
- 1.2.4. የውርርዱ ቦታ- ማለት ውርርዱ የተፈጸመበት ቦታ እና ጊዜ ሲሆን ይህም የውርርዱ መረጃ በመረጃ ቋት በድርጅቱ የመረጃ ማእከል የተመዘገበበት ማለት ነው፡፡
- 1.2.5. የመወራረድ እድል- ማለት ቀደም ብሎ ከተሰጡ ማይታወቁ ውጤቶች መሰረት የተወሰነ ተጨባጭነት ያላቸው እውነታ በመጨመር በውርርዱ ወቅት የተሻለ እድል የሚያስገኝ ግምት ማለት ነው፡፡ ይህ የእድል እና የግምት ወይም የእጣ ጉዳይ ሲሆን ሌሎች በድርጅቱ የተመረጡ ዝግጅቶች በውርረዱ ጽ/ቤት ታትመው እና ተዘጋጅተው የሚሰጥ ተያያዥ የተመረጠ የውርርድ ግምት ሲሆን ይህም በውርርዱ ጽ/ቤት ወይም በድርጅት የውርርድ መረጃ መረብ www.championbet.et ታትሞ የሚሰጥ የውርርድ ማስረጃ ነው፡፡ የውርርዱ እድል የምርጫዎች (የጉርሻዎች) እንዲሁም የተለያዩ ሊሆን ይችላል ተብሎ የሚሰጡ መላ ምታዊ ግምት የያዘ ይሆናል፡፡
- 1.2.6. የውርርድ ምርጫዎች (እድሎች) በውርርዱ እድሎች ምልክቶች አማካኝነት አስፈላጊ የውርርድ ምርጫዎች (እድል) ለይቶ መጠቀም የሚቻል ሲሆን ለምሳሌ፡-
| 1 | የባለሜዳ እድል |
|---|---|
| 1X | የባለ ሜዳ እድል ወይም እኩል እድል |
| X | እኩል እድል ማለት የትኛውም ተቀናቃኝ ሳያሸንፍ 0ለ0 ወይም 1ለ 1 ወይም 2ለ 2 እኩል መውጣት ማለት ነው፡፡ |
| 2X | ከሜዳው ውጪ ማሸነፍ ወይም እኩል እድል |
| 2 | ከሜዳው ውጪ ማሸነፍ |
| 12 | እኩል እድል የለም ማለት ከተወዳዳሪ ቡድኖች የግደ አንዱ ማሸነፍ ያለበት ሲሆን እኩል የመውጣት የለውም፡፡ |
| 1-4 | በመጀመሪያዎቹ አራት ውስጥ ማካተት |
| 2:1 | ተጨባጭ የውድድር ውጤት (ለምሳሌ 2ለ1) |
| V | አሸናፊ |
- 1.2.7. የይወራረዱ እድሎች አይነት- የይወራረዱ ኩባንያዎች የማሸነፍ ኦድ/ግምቶች እድል በአሸናፊው በማተም ሊያዘጋጁ የሚችሉ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን ከተወዳዳሪዎቹ ግለሰቢች ዌም ቡድን በአንዱ የስፖርት ውድድር ከፍተኛ ስብብሰብ በሆነ ቡድን ግምት ውስጥ ማካተት ወይም በረጅም ጊዜ የስፖርት ውድድር ባህሪ መሰረት አድርጎ ወይም በተጨባጭ ከስፖርት ውድድር ውጤት ጋር በቀጥታ ተግባር በማያያዝ ወይም የስፖርቱ ሂደት መሰረት አድርጎ ወይም ሌሎች ማህበራዊ እና ዝግቶች ግምት ውስጥ በማስገባት የውርርዱን የማሸነፍ እድል ሊያዘጋጁ ወይም ሊያሰሳትሙ ይቨላሉ፡፡
- 1.2.8. ኦዶች/ግምቶች ማለት በትክክል በተሳካ ሁኔታ ከተወዳደሪ አካላት አንዱ ያሸንፋል ብሎ የውርርድ ምርጫዎችን ማስቀመጥ ማለት ነው፡፡ የውርርድ ግምት ተቀባይነትየሚኖረው በመጀመሪ ውድድሩ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ የወቀረበ ሆኖ በሁለቱም ስምምነት ላይ የተመሰረተ ቢሆንም ግን የመጨረሻ ውቴቱን ከግምት ሳያስገቡ አስቀድሞ መተንበይ ወይም መገመትማለት ነው፡፡ ነገር ግን በተራ ቁጥር 3.6 የተዘረዘሩ ደንቦች ከዚህ አሰራር ውስጥ የተካከተቱ አይሆንም፡፡
- 1.2.9. ክፍያ- ማለት ውርርዱ ላሸነፈው ግለሰብ በግምቱ መሰረት ውርርዱን የሚመራው ድርጅት የሚከፍለው የአሸናፊነት ክፍያ ወይም የውርርዱ ማሸነፍ ክፍያ ማለት ሲሆን ይህም የሚፈጸመው ውርርዱን ያሸነፈው ግለሰብ በመረጣቸው ውርርድ እድሎች እና ግምቶች መሰረት በአተቃላይ የውርዱ ህጋዊ ውጠቶች መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ በውርርድ የሚከፈለው ክፍያ በስምምነቱ ህጊች እና ደንቦች መሰፈረት ሊቀንስ ይችላል፡፡
- 1.2.10. ህጋዊ ውጤት- ማለት በውርርዱ ባለቤት በሆነው ድርጅት በቀረበው የውርርድ ውጤት መሰረት የታተመ ወይም የቀረበ ሲሆን ይህም ከህጋዊ የመረጃ ምንጭ በተገበኙ ነመሰረት የሚቀርብ ይሆናል፡፡
- 1.2.11. ማወራረድ-ማለት ህጋዊ የውድድሩ ውጤት እና የውርርድ ውጤት የሚያንጸባርቅ ያሸነፈውን ውድድር ለመወሰን የሚቀርብ ይሆናል፡፡
- 1.2.12. ትኬት-ማለት በድርጅቱ የመረጃ ማእከል አስቀድሞ የውርርዱ ግምት በሚቀርብበት ጊዜ ታትሞ ለተወራረደው አካል ተመዝግቦ የሚሰጥ ነው፡፡ በትኬቱ ላይ የሞገኘው የመረጃ መረብም በደንበኛው አማካንነት በሚቀርበው መሰረት የሚታተም ይሆናል፡፡ በትኬቱ አንዱ መስመር ላይ ያለው ቢታ ውስን በመሆኑ እና ሌሎች ቃላቶች በተፈለገው ሁኔታ ለማካተት ውስን በመሆኑ ለውርርዱ እድል ማሳያ ተጠበቀና የሚቀመጥ ይሆናል፡፡ የተወዳዳሪው ቡድኖች ስም፣ የተወዳደሪዎች ስም ወዘተ በምህጻረ ቃል የሚጻፉበት ይሆናል፡፡ ብኬቱ ላይ ከሚቀርቡ መረጃዎች ተከትለውም፡- የውርርዱ አጠቃላይ ዝግጅቶች ዝርዝር፣ መደብ፣ የውርርዱ ኦዶች/ግምቶች፣ ምርጫዎች እና መረጃዎቹ እና የገባበት ሰአት በትክክለኛው እና ተጨባጭ አንድ ሰከንድ ልዩነትተመዝግቦ የሚቀርብበት ይሆናል፡፡
- 1.2.13. መተግበሪያ፡- የኮምፒዩተር መተግበሪያ ውርርዱን በሚያካሂደው ድርጅት ኮምፒውተር ላይ በቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶችም ሆነ በውርርዱ ክፍሎች ወይም ጽ/ቤቶች የሰፈሩ መተግበሪያዎች ሲሆኑ እነዚህም ደንበኛ የቀረቡ ውርርዶች የእነ ማን እንደሀሆኑ መለየት የሚችልበት መተግበሪያ ይኖራል፡፡
- 1.2.14. ድጋፍ ሰጪ የውርርድ እድሎች- ማለት ተመሳሳይ እና እኩል የሆነ የውርርድ አድሎች ወይም የውርርድ እድሎች ሲሆኑ እርስ በእርሳቸው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደጋገፉ ሲሆኑ ለምሳሌ፡-
- 1.2.14.1. በተወዳደሪ (ቡድኖች) የሚቀርቡ ውርርዶች በተመሳሳይ ሁኔታ በተወዳዳሪ በአሸናፊ ተወዳዳሪ ቡድኖች በተናጠል በተመሳሳይ ውድድር የመቀርብ ተመሳሳይ እድል
- 1.2.14.2. ተመሳሳ ተወዳዳሪ (ቡድን) በተለያዩ የእድሎች አጋጣሚ ወይም ቦታዎች ላይ ማስቀመጥ (“V”፣ 1ለ2፣ 1ለ3 ወዘተ) በአንድ የስፖርት ወድድር ስነስረአት የሚቀርብ
- 1.2.14.3. የተጠናቀቁ ውድድሮች ውጤት መሰረት የሚካሄደው የውርርድ ሂደት አስቀድሞ በተመሳሳይ ቡድን ውጤት የሚቀረብ ውርርድ ማት ነው፡፡
- 1.2.14.4. መተግበሪው ለደንበኛው የሚሰጠው ማሳሰቢያ ስለማንኛውም ስፖርታዊ ውርርዶች እና ሌሎች ለማስቀመጥ የማይፈቀዱትን ያካትታል፡፡ በስህተት እነዘህ ውርርዶች የቀረቡ ከሆነ ከፍተኛ ኦድ/ግምት የተሰጠው ስፖርታዊ የውርድ እድሎች አሸናፊውን ለመገመት የሚወሰዱ ሲሆን ሌሎች ስፖርታዊ ውርርድ ኦዶች ግን ሊወገዱ (ኦድ 1፣00) ይችላሉ፡፡
- 1.2.15. የስምምነት ህጎች እና ደንቦች- ማለት ስፖርታዊ ውድድር አስመልክቶ የሚካሄደው ውርርድ የሚመራበት ህጎች እና ደንቦች ማለት ናቸው፡፡
- 1.2.16. የውርርድ ጽ/ቤት ቅርንጫፍ- ማለት ውርርዱ የሚያስተበናግደው ድርጅት በቋሚነት የከፈተው መስሪያ ቤት ወይም ቅርንጫፍ ውርርዱን ለማከናወን እና ለማቅረብ እና ለአሸናፊዎች የሚከፈለውን ክፍያ ለመፈጸም የሚያገለግሉ ጽ/ቤት/ቅ/መስሪያ ቤት ነው፡፡
- 1.2.17. የአገልግሎት ሰጪ ሰራተኛ- ማንኛውም ስፖርታዊ ውርርድ የሚካሄድበት እና ስፖርታዊ ውርርድ ክፍያ የሚፈጸምበት በህጋዊ መንገድ ውርርዱን ለማካሄድ በተፈቀደለት ድርጅት አማካኝነት የተቀጠረ ሰራተኛ ወይም ግለሰብ ማለት ሲሆን በዚህ መሰረትም ሰራተኛው ወይም ግለሰቡ ከ18 አመት በላይ የሞላት ወይም የሞላው መሆን ያለበት ሲሆን ግለሰቡ/ግለሰቧ የዚህን ውርርድ ህጎች እና ደንቦችን ተከትሎ መስራት የሚችል መሆን ይገባል፡፡
- 1.3. ለስፖርታዊ ውርርድ ውስጥ ለመሳተፍ የሚያስችሉ የስምምነት ደንቦች
- 1.3.1. በስፖርታዊ ውርርድ ሂደት ውስጥ መሳተፍ የሚችል እና መወራረድ የሚፈቀደወው እድሜያቸው ለ21 አመት በላይ የሆናቸው ግለሰቦች ብቻ ሲሆኑ በውርርዱ ቦታ ከተጠቀሰው አመት በላይ የሆናቸው ብቻ መገኘት ይችላሉ፡፡ ደንበኛው ከስፖርታዊ ውርርድ ህጎች እና ደንቦች ጋር የተላመደ እና ስለ ህገቹ እና ደንቦቹ በቂ እውቀት ያለው ሊሆን ይገባል፡፡
- 1.3.2. የስፖርታዊ ውርርድ በምናቀርብበት ጊዜ ወይም ክፍያ ለመቀበል በምንቀርብበት ጊዜ እያንዳንዱ ደንበኛ ውርርዱን ስለማሸነፉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ለአገልግሎት ሰጪው ሰራተኛ በተጠየቀበት ጊዜ ሁሉ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ድርጅቱ የሚወራረድበትን ማቅረብም ሆነ ተወራርዶ ያሸነፈበትን ገንዘብ ህጉ በፈቀደው ሁኔታ የመገደብ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
- 1.3.3. ኩባንያው የደንበኛውን የውርርድ ማቅረቢያ የመቀበል ግዴታ የሌለበት ሲሆን በተለይ በመጠጥ ስካር፣ ወይም በመልካም ባህሪ ከሚቀርቡ ደንበኞች ወይም የስፖርታዊ ውድድር ህጎችና ደንቦችን በሚጥስ መልኩ ከሚያቀርቡ ደንበኞች የመቀበል ግዴታ የለውም፡
2. የውርርዱ አይነት
- 2.1. የውርርዱ አይነት
- 2.1.1. አኮ ውርርድ- ማለት በተመሳሳይ ጊዜ አንድ ወይም ከዛ በላይ የሆኑ የውርርድ እድሎችን ማቅረብ ማለት ነው፡፡ በአኮ ውርርድ ሂደት ውስጥ የመጨረሻ ማጠቃለያ ኦድ/ግምት አጠቃላይ በትኬቱ ላይ ተመርጦ የቀረቡትን እድሎች/ኦዶችን በማባዛት የሚገኝ ኦድ/ግምት ይሆናል፡፡ የማጠቃለያ ኦድ/ግምት አብዛኛው ጊዜ በባለ ሁለት ዲጂት ወደ ሚቀርበው አሃዝ የሚጠጋጋ ሆናል፡፡ ሶስተኛው ለመጠጋጋት አመቺ ሆነ ዲጂት የሚገኝ ከሆነ የሚወሰደው ቁጥር 5 ይሆናል፤ የማጠቃለያ ኦዶች/ግምቶች ግን ወደሚቀርባቸው ቁጥሮች ወይም ወደሚጠጋጉ ቁጥሮች የሚጠጋጉ (ለምሳሌ፡- 3125 ወደ 3፣13 የሚጠጋጋ) ይሆናሉ፡፡ ትኬቱ ላይ ማሸነፍ የሚቻለው ሁሉም በትኬቱ ላይ የቀረቡት የማሸነፍ እድሎች በትክክል የተቀመጡ ከሆነ ብቻ ነው፡፡
- 2.2. የውርርድ እድሎች አይነት
- 2.2.1. የውርርድ እድሎች በሁለት ውጤቶች ላይ የተመሰረቱ (ለምሳሌ፡- የቴኒስ፣ የቮሊቦል)
- 2.2.2. የውርርድ እድሎች በሶስት ውጤቶች ላይ የተመሰረቱ (ለምሳሌ፡- የእግር ኳስ፣ የበረዶ ላይ ሸርተቴ)
- 2.2.3. በማሸነፍ ወይም አሸናፊ ግለሰቦች ወይም ቡድኖችን በማቅረብ የሚካሄደው ስፖርታዊ ውርርድ እደሎች (ለምሳሌ፡- ቀመር 1)
- 2.2.4. ሌሎች የውርርድ እድሎች- ከሌሎች አጠቃላይ የውርርድ እድሎች የሚከተሉትን በትኬቶች ላይ የሚቀርቡ የውድድር አይነቶችን መጥቀስ ይቻላል እነዚህም፡- በትክክለኛው የውርርድ ውጤት ላይ የተመሰረተ፣ በማቅረብ የሚካሄድ ውርርድ፣ በውድድሩ ሂደት ላይ የተመሰረተ ውርርድ፣በመጀመሪያ ተዘጋጅቶ በቀረበው ላይ የሚቀርብ የውርርድ አይነት፣ የአካል ጉዳተኞች ውድድር ውርርድ ወዘተ መጥቀስ ይቻላል፡፡
3. ውርርድ እና ኦዶች/ግምቶች
- 3.1. አጠቃላይ ደንቦች
- 3.1.1. ኦዶች/ግምቶች በተለያዩ ለውጦች መሰረት ይወሰናሉ፡፡ የውርርድ ትኬት ከቀረበ በኋላ ድርጅቱ ማንኛውንም ኦድ የመቀየር መብቱ ተጠበቀ ነው፡፡
- 3.1.2. የስፖርታዊ ውርርድ ኦዶች/ግምቶች በውርርድ ጽ/ቤት በድርጅቱ የመረጃ መረብ www.championbet.et ይታተማል፡፡ ኦዶች/ግምቶች በሚለወጡበት ጊዜ በድርጅቱ ማእከላዊ ሰርቨር የተመዘገበው የመረጃ መረብ ህጋዊነታቸው እንድረጋገጥ ይደረጋል፡፡
- 3.1.3. መደብ ለአኮ ስፖርታዊ ውርርድ ዝቅተኛው የመደብ መጠን ብር 10 ነው፡፡ ለኮንቢ ስፖርታው ውርርድ ደግሞ ዝቅተኛው መደብ ብር 10 በየትኬቱ ሶሆን ለእያንዳንዱ የውርርድ አይነትም ዝቅተኛው መደብ (1-አኮ፣ 2-አኮ፣ 3-አኮ፣ 4-አኮ ወዘተ) ብር 30 ወይም ዚሁ ኢንቲጄራዊ ብዜት ይሆናል፡፡ ለእያንዳንዱ የስፖርት ውርርድ አይነት ድርጅቱ ከፍተኛ መደብ እንዲፈቀድ ሊወስን የሚችል ሰሆን የዚህ ለውጥ በተመለከተ በህትመት አዘጋጅቶ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡ ከፍተኛ የመደብ ጣርያ በከፍተኛ ክፍያ (ከጥሎ እንደምትመለከቱት) የተወሰነ ይሆናል፡፡ ድርጅቱ ከፍተኛ የመደብ ጣርያ በአንድ አንድ ለየት ባሉ ውድድሮች ላይ ላይገድብ ይችላል፡፡
- 3.1.4. የውርርድ እድሎች ቁጥር- በአኮ የውርርድ ጨዋታ ጊዜ ማንኛውም ደንበኛ የፈለገውን ማንኛውንም የውርርድ ቁጥር መምረጥ ይችላል፡፡
- 3.1.5. በዋናው ውድድር ማሸነፊያ- የዋናው ውደድር ውርርድ ጨዋታ ማሸነፍ የሚቻለው ሌላ ምንም አይነት አሰስተያት በተለየ መልኩ ካልተሰጠበት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በይበልጥ ከውርርድ ጨዋታ አይነቶች ጋር የተያያዘ ነው (ለምሳሌ፡- ቀመር 1) ወይም እጅግ በተሸለ አፈጻጸም (ለምሳሌ ለአትሌቲክሶች)፡፡
- 3.1.6. የክፍያው ገደብ፡- በአኮ የውርርድ ጨዋታ አይነት ከፍተኛ የሽልማት ከፍያ በ1,000,000.00 ሚሊየን ብር የተገደበ ነው፡፡
- 3.1.6.1. በዚህ የውርርድ ጨዋታ አይነት ከተጠቀሰው ገንዘብ በላይ ላሸነፈው ደንበኛ ክፍያ ከተቀመጠው ገደብ በላይ የማይፈጸም ሲሆን ደንበኛውም ከዚህ በለይ ለሆነ ክፍያ በህጉ መሰረት መጠየቅ መብት አይኖረውም፡፡
- 3.1.7. ውርርዱም የሚያካሄደው ወይም የሚያጫውተው ኩባንያ ዝቅተኛውን እና ከፍተኛ የውርርድ ጣርያ የመወሰን መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ይህም ደግሞ የውርርዱ እድሎች ጨዋታ ከመጀመሩ ከተጠበቀ ጊዜ ቀደም ብሎ በማሳወቅ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ በእርግጥ የውርርዱ ጊዜ እና ሁኔታ ደንበኛው በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ውስጥ መወሰን ያለበት ሲሆን ይህም ውርርዱ እንዲቆም ከታዘዘ በኋላ መለወጥ ወይም በተለየ ሁኔታ እንዲለወጥ ማድረግ የማይቻል ሲሆን አንዴ ከተቀበለ በኋላ የመጨረሻ ተቀባይት ውሰዳኔ የሚያገኘው የውርርዱ ጨዋታ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ ከቀረበ ብቻ ነው፡፡
- 3.2. ውርርድ ስለማቅረብ
- 3.2.1. የሚቀርቡ ውርርዶች የውርርዴን ጨዋታ በሚያጫውረቱ ሰራተኞች አማካኝነት ድርጅቱ በሚያሳትመው የውርርድ ማሸነፍ ግምቶች/ኦዶች መሰረት የሚቀመጥ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወይም በአንዳንድ ሁኔታዎች ውርርዱ በተፈቀደ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ጉዳይም ደግሞ ለደንበኛው በሰአት የሚገለጽ ሲሆን ይህንንም የውርርዱ አጫዋች አካል ለደንበኛው አስቀድሞ የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡ መደቡ በሚለወጥበት ጊዜ በተለወጠው መደብ መሰረት ደንበኛው የውርርድ ጨዋታውን የማስገባት ውሳኔ መወሰን ይችላል፡፡ ውርርዱ የተካሄደበት ጨዋታ ውድድር ከመጀመሩ 10 ደቂቃ ቀደም ብሎ የተቆረጠው ወይም የውርርዱን ጨዋታ ትኬት መሰረዝ ይቻላል፡፡
- 3.2.2. በዚህ ወቅትም ደንበኛ ለሰራተኞቹ የሚከተሉትን ነጥቦች ሪፖርት ደርጋል፡-
- 3.2.2.1. ታትሞ በተሰጠው መሰረት የውርርዱን ጨዋታ እድሎች ቁጥር
- 3.2.2.2. የመረጠው ውጤት እድል
- 3.2.2.3. መደቡን
- 3.2.3. አገልግሎት የሚሰጡ ሰራተኞች የቀረበላቸውን መረጃ በኮምፒውተር ውስጥ ካስገቡ በኋላ ትኬቱን አትመው ለደንበኛው የሚሰጡ ሲሆን ይህንን የሚሰጡም ደንበኛው የተጫወተበትን መደብ በሙሉ ከከፈለ በኋላ ይሆናል፡፡ ደንበኛው መረጃዎች በትክክል ከተረጋገጠ በኋላ ዝርዝሮቹ እና ደንበኛው ክፍያውን ከፈጸመ በኋላ ሰራተኛው ትኬቱን አትሞ ለደንበኛው የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ውርርዱን ካስገባ በኋላ እና ትኬት ከተቀበለ በኋላ ደንበኛው በዚህ የውርርድ ጨዋታ ህገ ደንብ የተስማማ መሆኑ ይታወቃል፡፡
- 3.2.4. ደንበኛው የሚያቀርበው መደብ መጠን ከውርርዱ ጨዋታ ህገ ደንብ አንጻር ያልቀረበ ከሆነ ወይም ህገ ደንቡን የሚጻረር ከሆነ (የመደቡ መጠን፣ ከፍተኛ የማሸነፍእድል ክፍያ ወዘተ) ጋር ተያይዞ ከውድድሩ ህግ እና ደንብ ጋር የሚጻረር ከሆነ ስለ ጉዳዩ ሰራተኛው ለደንበኛው በማሳወቅ እንደገና መደቡን አሻሽሎ በተነገረው መሰረት ከከፈለ በኋላ እና መስፈርቱን አሟልቶ ካቀረበ በኋላ የውርርዱ ጨዋታ ገቢ ተደርጎ ተቀባይነት የሚያገኝ ይሆናል፡፡
- 3.2.5. ደንበኛው አስፈላጊ የሆኑ የማረጃ ቋቶች በትኬቱ ላይ የተሟሉ መሆናቸው እና ተሟልተው መቅረባቸውን እና በሰጣቸው መረጃዎች መሰረት ማቅረባቸውን የማረጋገጥ ሃላፊነት ይኖረዋል፡፡ ደንበኛው ተቆርጦ በሰጠው ትኬቱ ላይ ስህተት ካስተዋለ ወይም ካገኘ ወዲያው ለሰራተኛው ሪፖርት በማድረግ እንዲስተካከል ይደረጋል፡፡ ይሁን እንጂ ከ10 ደቂቃ በኋላ የሚቀርብ ቅሬታ ወይም ከትኬቱ ጋር ተያይዞ የሚቀርበው ቅሬታ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- 3.2.6. እንዲሁም ከዚህ በተጨማሪ የተመላሽ ገንዘብ ትክክለኛነት የማረጋገጥ ሃላፊነት የደንበኛው ይሆናል፡፡ ዘግይቶ ቅሬታ ማቅረብ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- 3.2.7. በደንበኛው የሚቀርበው የውርርድ ቁጥር ገደብ የማይኖረው ሲሆን ግን የውርርዱን ቁጥር በተለያዩ ሁኔታዎች አሻሽሎ እና ቀይሮ ማቀረብ ለውጥ (የጨዋታው ውድድር ግምቶች/ኦዶች ለውጥ፣ የውርርዱን ጨዋታ ውድቅ ማድረግ ወዘተ) ሊያስከትል ይችላል፡፡
- 3.2.8. ትኬቱ ተቆርጦ ከተሰጠ በኋላ በትኬቱ ላይ ማንኛውም አይነት ለውጥ ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ እንዲሁም በውሸት ወይም ትኬት ላይ የማጭበርበር ድርጊት እና የማይገባ የይገባኛል ክፍያ ጥያቄ ማቅረብ ፈጽሞ የተከለከለ ሲሆን ትኬቱም በዚህ ምክንያት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- 3.2.9. በኢትዮጵያ ህግ እና አግባብነት ወይም ተያያዥነት ባለው የሎተሪ ህግ መሰረት የእኛ ድርጅትም 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል፡፡ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከሚቀርበው የውርርድ ጨዋታ ተቀናሽ ይሆናል፡፡ የትክክለኛው ትኬት ሁኔታዎች (3.2.9.1) ተመልክቷል፡፡
- 3.2.9.1. የውርርድ ጨዋታ ማስገባት ምሳሌዎች
- 3.3. ህጋዊ ውጤቱ እና የውርርዱ ማወራረድ
- 3.3.1. ሁሉም ህጋዊ የውድድር ጨዋታ ውጤቶች በድርጅቱ ለዚሁ መተግበሪያ በተዘጋጀው የሚታተም ሲሆን በውርርዱ ጽ/ቤቶች ታትሞ ይቀርባል፡፡ የታተመው የውርርዱ ጨዋታ ውጤት ትክክል ካልሆነ ደንበኛው ያሸነፈበትን የመጠየቅ መብቱ በትክክል ውጤቱ አረጋግጦ ካቀረበ በምንም አይነት መልኩ የመጠየቅ መብቱን አይጋፋም፡፡
- 3.3.2. ቀደም ብሎ የጨዋታ ጊዜያቸው የተወሰኑ ከሆነ (ለምሳሌ የእግር ኳስ ውድድር) ህጋዊ የውድድሩ ውጤት በሜዳው ላይ በተጨባጭ የታየ ውጤት ይሆናል፡፡ ከዚህ ግምት አንጻርም ውድድሩ በተቀመጠለት የውድደር ጊዜ እና ሰአት በሙሉ ተከናውኖ ተጠናቀቀ መሆን አለበት ሲሆን በዚህ አይነት የውርርድ ጨዋታ ሂደትም (ከመጀመሪያው 1 ደቂቃ ጀምሮ፣ ያለምንም ተጨማሪ ጊዜ፣ የቅጣት ኳስ መስተት ወዘተ) እና በተገቢው ሁኔታ መጠናቀቅ ይገባል፡፡
- 3.3.3. በውድድሩ ሰአት እና ጊዜ ያላላቀ ከሆነ በተቋረጠበት ሰአት በነበረው ውጤት በሚያሻማ መልኩ ለመገመት የሚያስችል በመሆኑ በተቋረጠው ጊዜ (ለምሳሌ፡- በመጀመሪያው ግማሽ ሰአት የነበረው ውጤት፣ ጎል ያስቆጠረው ቡድን፣ የጎሎች ብዛት ወዘተ) መሰረት የሚወራረድ ይሆናል፡፡
- 3.3.4. በማንኛውም ሰአት ጎል ያስቆጠረው ቡድን መሰረት አድርጎ በራስ ግምት የሚቀርቡ ጎሎች የጨዋታውን ውጤት መሰረት አድርጎ ለማወራረድ ከግምት ውስጥ አይገቡም፡፡
- 3.3.5. ውጤቶች እና አጠቃላይ ውድድሮቹ የውድደድሩ ሙሉ አካል ሆነው ይቆጠራሉ፡፤ ስለዚህ ተወዳዳሪ (ወይም ቡድኑ) በዚህ ውጤት እና አጠቃላይ ውድድሩ ውስጥ ተሳትፎ ካደረገ ነገር ግን ለዋናው ውድድር ብቁ ምክንያት ካልሆነ በዚህ ረገድ የቀረበው የውርርድ ጨዋታ ውድቅ እንደተደረገ ይቆጠራል፡፡
- 3.3.6. በቴኒስ ውድድር የሚካሄደው ውርርድ በሌላ ሁኔታ ወይም አከባቢ ውድድሩ የተካሄደ እንደሆነ እንደተሸረ አይቆጠርም፡፡
- 3.3.7. ውድድሩ በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ የተጠናቀቀ እንደሆነ ከዛ በኋላ የሚቀጥለው (በዲስኳሊፊኬሽን ምክንያት ወይም በአበረታች መውሰድ ምክንያት ወዘተ) ወይም እንደገና በድጋሚ በሚታየው ጨዋታ የሚፈጸም ከሆነ ውጤቱ በጨዋታው ሜዳ ላይተግባራዊ ይደረጋል፡፡ ለጨዋታው ውርርድ አይነት ህጋዊ ለማድረግ ወይም ለማረጋገጥ (ለምሳሌ፡- የዋንጫ ውድድር) የዳኛው የመጨረሻ ማጠቃለያ ውሳኔ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ነገር ግን ቅሬታ የቀረበበት ከሆነ (ወይም ሊህ የጨዋታ ውድድር አይነት ትክክለኛ አስተዋጽኦ ሊያበረክት የሚችል ድርጊት ከተፈጸመ) የጨዋታው አሸናፊዎች ከመጀመሩ በፊት ለመክፈል የሚደረገው ጥረት በዳኛው የመጨረሻ ውሳኔ መሰረት ተግባራዊ ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በዚህ አይነት ድርጊት ተግባራዊ የሚደረጉ የጨዋታው ጊዜ አስቀድሞ ካልተገመተ ነው፡፡ ማንኛውም ተጨማሪ የጎል ለውጥ የሚደረገው ከግምት ውስጥ አይገባም፡፡
- 3.3.8. በተለያዩ ጨዋታዎቹ በመቋረጣቸው በውጠት ላይ የሚደረገው ለውጥ ለምሳሌ በዲስኳሊፊኬሽን ምክንያ፣ በአበረታች መድሃኒቴ በመጠቀም ምክንያት ወዘተ ከግምት ውስጥ አስገብቶ ጨዋታው ወይም የውድድሩ ውጤት ላይ ለውጥ የሚያስከትሉ ድርጊቶች በተፈጸሙ ጊዜ ለውርርዱ ያልተከፈለ ክፍያ በዋናው ውጤት መሰረት የሚከፈል ይሆናል፡፡
- 3.3.9. ጨዋታው በመዘዋወሩ ወይም በመተላለፉ ምክንያት ከ3 ቀናት በኋላ የሚካሄድ ውድድር አስመልክቶ ድርጅቱ የእነዚህን የውድድር መወራረድ መሰረት ውርርዶቹን የመሰረዝ መብቱ ጠበቀ ይሆናል፡፡ ውድድሩ ከተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ቀደም ብሎ ውድድሩ የጀመረ እንደሆነ የውድድሩ ሂደት ከመጀመሩ በፊት የወረቡ ውርርዶች ህጋዊ ይሆናሉ፡፡
- 3.3.10. የውርርድ ጨዋታው ትኬት በታተመበት ወቅት የቤዝ ቦል ውድድር በማንኛውም ምክንያት ያልተከናወነ ከሆነ በዚህ ጨዋታ የቀረቡ የውርርዱ ትኬቶች በሙሉ የሚሰረዙ ይሆናሉ፡፡ 2 የተለያዩ ቡድኖች በመደዳ በአንድ ቀን 2 የተለያዩ ውድድሮችን ከተጫወቱ የውርርዱ ጉዳይ ተፈጻሚነት የሚኖረው ምንም ጊዜም በመጀመሪያ በተካሄደው ውድድር ብቻ ይሆናል፡፡
- 3.3.11. ጨዋታው በተለያዩ ምክንያቶች ከተቋረጠ ወይም በዲስኳሊፊኬሽን ዝርዝር (የጨዋታው ግምቶች/ኦዶች ከታተሙ) ተወዳዳሪ ወይም ቡድን (ለምሳሌ፡- ቀመር 1) የውርርዱ ውጤት ማሸነፍ የማይቻል ነው፡፡ ተወዳዳሪው ወይም ቡድን ሙሉ በሙሉ በውድድ ላይ ካልተሳተፈ በዚህ ረገድ የቀረበው የውርርድ ጨዋታ እድል የሚሰረዝ ይሆናል፡፡
- 3.3.12. በተለያዩ ምክንያቶች የቴኒስ ውድድር መቋረጥ ህጎች የሚከተሉት ይሆናሉ፡-
- 3.3.12.1. በተለያዩ ምክንያቶች የቴኒስ ውድድሩ ከተቋረጠ በዚህ ረገድ የቀረቡት ውርርዶች በሙሉ (ግምቶች/ኦዶች 1፣00) የሚሻር ወይም የሚሰረዝ ይሆናል፡፡
- 3.3.12.2. የመጀመሪያው የውድድሩ ክፍል ወይም ምእራፍ ከተጠናቀቀ ውጤቱ አስቀድሞ ከታወቀ ሁሉም የውርርዱ አይነቶች በዚህ መልኩ የሚወራረዱ ይሆናሉ፡፡ በውድድሩ ኦዶች/ግምቶች በተጫዋች የቀረቡ ውርርዶች ከተቋረጠ እንደተሸነፈ የሚቆጠር ይሆናል፡፡
- 3.3.13. የታተመው ውጤት በግልጽ በትክክል ያልታተመ መሆኑ ከተረጋገጠ በዚህ ረገድ የሚቀርበው ማንኛውም ቅሬታ ከግምት ውስጥ ገብቶ ምላሽ የሚሠጥበት ይሆናል፡፡ በዚህ አይነት አሰራርም የውርርዱን ማሸነፍ ክፍያ ውጤቱ ወዲያው እንደተስተካከለ እንዲከፈል ይደረጋል፡፡
- 3.3.14. ህጋዊ እና ትክክለኛ ውጤቱ ከተገለጸ በኋላ የተወራረደው ቅሬታ በዚሁ መልኩ የሚሰላ ሲሆን ሌላ አይነት የውጤት ማስተካከያ አይኖረውም (የተረጋገጠ የአበረታች መድሃኒት መጠቀም ወዘተ) ከግምት ውስጥ የሚገባ ነው፡፡
- 3.3.15. ውድድሩ ከተቋረጠ ወይም ካጠረ (ለምሳሌ በቀመር 1) የተገኘው ውጤት እና አጠቃላይ ቀረቡ የውርርዱ ጨዋታ ስልጣን በተሰጠው አካል በተወሰነው መሰረት (አስቀድሚ ከተተነበየ ወይም አስቀድሞ የጨዋታው ጊዜ ከተተነበየ በስተቀር) መሰረት ተግባራዊ ይሆናል፡፡
- 3.3.16. ከአንድ ውድድርበላይ በአንድ ቦታ በአጭር ጎዜ ውስጥ ከተካሄደ የዚህ አይነቱ የውርረድ ሁኔታ ምንም ጊዜም በመጀመሪያው ውርርድ ላይ ተፈጻሚ ጠይሆናል፡፡
- 3.3.17. የውርርዱን እድሎች በመለስተኛ ስህተት ወደመተግበሪያከገባ በኋላ ለምሳሌ እንደ የተወዳዳሪው የተሳሳተ ስም፣ የቡድን ወይም የውድደሩ ስም የተሳሳተ መሆን በውጤቱ ላይ ምንም አይነትለውጥሳያስከትል በዚህ ረገድ የቀረቡ ውርርዶች በሙሉ ተቀባይነት የሚኒረፋቸው ይሆናል፡፤
- 3.4. የአሸናፊ ባለቤት
- 3.4.1. የሚከተሉት ሁኔታዎች በሙሉ ከተሟሉ የደንበኛው አሸናፊነት የሚረጋገጥ ይሆናል፡-
- 3.4.1.1. የውርርዱ ጨዋታ በትክክል ውሳኔ ገኘ ከሆነ
- 3.4.1.2. በአኮ ውርረድ አይነት ሁሉም ውርርዶች በትክክል ከቀረቡ
- 3.4.1.3. የውርርዱ ህጎች እና ደንቦች በምንም አይት መልኩ ያልተጣሱ ሆነው ከቀረቡ
- 3.4.2. ህጋዊ ውጤቶች ከታተመ በኋላ ከህጋዊ ውጤት መታተምበፊት የሚቀርበው ቅሬታ ወይም ተቃውሞ በድርጅቱ አማካኝነት ድርጅቱ ከማተሙ በፊት የቀረቡ ከሆነ አስፈላጊ የገንዘብ ማሸነፍ ውጠት በመጨረሻው ውሰዳኔ ከተሰጠ በኋላ መከፈል ይጀምራል፡፡
- 3.4.3. ጠቅላላ የማሸነፍ ውጤት በሁሉም የውርርድ አይነቶች በተወዳደሪ ቡድን ወይም ግለሰብ አማካኝነት የሚቀነስ ሲሆን ይህም የሚቀነሰው በአንድ ቦታ ሁለት እና ከዛ በላይ ውድድሮች የተጠናቀቁ ከሆኑ ነው፡፡ የውርርዱ ጠቅላላ የማሸነፍ እድል በተመሳሳይ ጊዜ በተመሳሳይ ሁኔታ ባጠናቀቁ ቡድኖች/ግለሰቦች መሰረት አድርጎ የሚካፈል ይሆናል፡፤
- 3.5. ክፍያ
- 3.5.1. በአንድ ትኬት ከፍተኛ የማሸነፍ ጣርያ 1,000,000.00 ነው፡ የሁሉም የውርርድ ውጤቶች ህጋዊ ውጤት በትክክል ከተገለጸ በኋላ በትኬቱ ላይ ያለው መረጃ መሰረት አድርጎ ክፍያው ከታተመ በኋላ በድርጅቱ እንደሚከተለው ይከፈላል፡-
- 3.5.2. ምናልባት ከላይ የተገለጸ የገንዘብ መጠን የሌለ ከሆነ በድርጅቱ የክፍያው ጊዜ እስከ 160 ቀናት እንዲሰጥ ማድረግ ይቻላል፡፡ የክፍያው ጊዜም የሚጀምረው በትኬቱ ላይ የመጨረሻ ምርጫ ከተወራረደ በኋላ የሚጀመር ይሆናል፡፡ አሸናፊዎች በጥሬ ገንዘብ በሰራተኞቹ ክፈያቸውን ያገኛሉ፡፡ በሚከፈለው ገንዘብ መጠን ላይ ቅሬታ ያለው አሸናፊ በ30 ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ አስፈላጊው ማስተካከያ አድርጎ ክፍያውን የመፈጸም ግዴታ ይኖርበታል፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላ ግን በአሸናፊዎች የሚቀርቡ ክፍያዎች ወይም የክፍያ ጥያቄዎች ውድቅ ይደረጋሉ፡፡ ቅሬታ ከቀረበበት ቅሬታው የመጨረሻው ውሳኔ እስከሚሰጥ ጊዜ ድረስ የሚቋረጥ ይሆናል፡፡
- 3.5.3. የውርርዱ መረጃዎች በኩባንያው ማእከላዊ የመረጃ ቋት ሰርቨር ላይ የሚቆዩ ሲሆን አስፈላጊውን ሁሉ መረጃዎች ለማስተካከያ ጥያቄ ሲቀርብባቸው ከዚህ አንጻር ታይቶ የሚረጋገጡ ይሆናሉ፡፡
- 3.5.4. ያሸነፉበት ገንዘብ መጠን በትክክል ስለመከፈሉና ያለመከፈሉን የማረጋገጥ ሃላፊነት የደንበኛው ይሆናል፡፡ ገንዘቡን ተከፍሎት ከሄደ በኋላ የሚቀርበው ማንኛውም ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- 3.5.5. በኢትዮጵያ ህግ እና ተያያዥነት ባለው የሎተሪ ህግ መሰረት አስፈላጊው የገቢ ግብር 15 በመቶ ከመቶ ብር ጀምሮ ከዛ በላይ ከሞያሸንፉ አሸናፊዎች በአግባቡ ተቀንሰው ለሚመለከተው የመንግስት ባለስልጣን ገቢ የሚደረግ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ይህ ከአጠቃላይ ካሸነፉት ገንዘብ ተደምሮ የሚሰላ ይሆናል፡፡ ከ100 ብር በታች ያሸነፈው ላይም ምንም የሚቆረጥ ግብር አይኖርም፡፡ ከ100 ብር በላይ ካሸነው አሸናፊ 15 በመቶ ግብር ይቆረጣል፡፡ የአሸናፊ ትኬቶች ትክክለኛ ስሌት እንደሚከተው (3.5.5.1.፣ 3.5.5..2.) ተመልከተዋል፡፡
- 3.5.5.1. ለምሳሌ የአሸናፊ ትኬት አፈጻጸም፡- አሸናፊ ፡- ብር 800 ገቢ ግብር (በሎተሪነኮሚሽን ግብር) 0 በመቶ፣ 0 ብር (ከ1000 በታች ክፈያ አሸናፊ፣ የገቢ ግብር 0 በመቶ) የተጣራ የአሸናፊ ክፍያ ብር 800 ብር
- 3.5.5.2. ለምሳሌ የአሸናፊ ትኬት አፈጻጸም፡- አሸናፊ ፡- ብር 1500 ገቢ ግብር (በሎተሪ ኮሚሽን ግብር) 15 በመቶ፣ 225 ብር (ገቢ ግብር 15 በመቶ የሚሆነው 225 ብር) የተጣራ የአሸናፊ ክፍያ ብር 1275 ብር
- የውርርዱ ተመላሽ ክፍያ
- 3.6.1. በውርርድ የተገኘው ገንዘብ ተመላሽ የሚደረገው ወይም ውድቅ የሚደረገው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፡፡
- 3.6.1.1. አስቀድሞ በተገለጸ የጨዋታ ጊዜ ውስጥ ውድድሩ ከተካሄደ ወይም ሌሎች አስቀድሞ የተተነበዩ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ (የዝግጅቱ ቁጥር ወዘተ) ከተከሰቱና በእነዚህ ጊዜ ወስጥ ውድድሩ ካልተካሄደ እና በተለያዩ አሰቀድሞ መገመት በማይቻል ምክንያት፣ በጭጋግ የኤሌክትሪክ ችግር፣ የተነመልካቾች ወይም ወዘተ ችግሮች ምክንያት ጨዋታው ከተቋረጠ እና በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ውድድሩ ካልተከናወነ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሌሎች ተመሳሳይ ውርርዶችም የሚሰረዙ ይሆናል፡፡ ውርርድ ተቀባይነት የሚኖረው በማየያሻማ መልኩ በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ውስጥ ከተከናወነ ወይም ሳይቋረጥ ከተካሄደ ብቻ ይሆናል (ለምሳሌ የግማሽ ጨዋታ ክፍለ ጊዜ ውጤት፣ ጎል አስቀድሞ የሚያስቂጥር ቡድን፣ የጎል ብዛት ወዘተ)
- 3.6.1.2. ባለሜዳው ቡድን በተሳሳተ መልኩ ከተገለጸ (ለምሳሌ፡- በእግር ኳስ ውድድር) በዚህ አይት ውድድር ውጤቱ ምንም ሆነ ምን ውድድሩ አስመልከቶ የተካሄዱ ውርርዶች የሚሻሩ ይሆናል፡፤ ይህ ህግ እና ደንብ ግን በሌላ ገለልተኛ ወገን ሜዳ ላይ በሚከናወኑ ውድድሮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡ እንዲሁም በዚህ ሜዳ ውድድሮች እንዲካሄዱ ከተወሰነ ያለተመልካቾች በሚካሄዱ ውድድሮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡ በጊዜ ቀመር እና ቦታ ላይ በሚደረጉ ለወውጦች ምክንያት ውርርዱ ላይ የሚስከትለው ሌላ ተጽእኖ አይኖርም፡፡
- 3.6.1.3. በድርጅቱ ውርርዱ እድል ቁጥር ተሳስቶ ከተመዘገበ ወይም በአስገዳጅ ሁኔታ የገባው መረጃ የጠፋ ከሆነ (በውድድሩ ወዘተ ህጎች ላይ በሚደረጉ ለውጦች) ከሆነ በዚህ ረገድ የነሚካሄዱ ውርርዶች የሚሻሩ ይሆናሉ፡፡ የተያዘው ገንዘብም ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- 3.6.1.4. ትክክለኛው ውድድር ከተጀመረ በኋላ በ3 ቀናት ውስጥ ከሆነ በዚህ ረገድ ውርርዱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ይህ አጋጣሚ ሲፈጠር ኩባንያው በ3.9 የተገለጸውን ደንብ ተግባራዊ ማድረግ ይችላል፡፡ ውርርዶቹም በሙሉ ሻራሉ፡፡
- 3.6.1.5. ለውርርድ ተያዘ ገንዘብ በታሻለ አገባብ እና በውርርዱ አይነት ተመላሽ ሊደረግ የሚችል ሲሆን ሁለቱም ተወዳዳሪዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ያልተመደቡ ከሆነ ውም በተመሳሳይ ቦታ የሚጠናቀቅ ከሆነ እና የእኩል እድል ግምት/ኦድ ያልተዘጋጀ ከሆነ
- 3.6.1.6. ውድድሩ ካሄዳል ተብሎ ከተቀመጠው ጊዜበኋላ ውርርዱ የቀረበ ከሆነ
- 3.6.1.7. ኩባንያው የማሸነፍ ሀግምቶች/ኦዶችን በተሳሳተ መልኩ ካስገባ ወይም ካጎደለ ወይም የጎል መስመር ወዘተ ከተሳሳተ
- 3.6.2. በአኮ የውርረድ ጨዋታ ከጥቅም ውጪ ወይም የሚሻሩት ወይም ተቀባይነትየማይኖራቸው ሁሉም የተመረጡ ውርርዶች ተቀባይነት ከሌላቸው ወይም በትክክል ካልቀረቡ ነው፡፡ በሌላ መንገድ በአኮ ውርርድ ተቀባይነት የሚኖራቸው አጠቃላይ ተቀባይነት የሌላቸው የተመረጡ ውርርዶች ከውርርዱ ዝርዝር ውስጥ ከተሸሩ እና አሸናፊዎች በእዚህ የውርርድ እድሎች አማካንነት ያለአሸናፊ ግምት ወይም ኦድ የሚሰሉ ከሆነ የሚሻሩ ይሆናል (ኦዱ/ግምቱ 1፣0 ከሆነ)
- 3.6.3. በኩባንያው የቀረበው በተሳሳተ መንገድ ከሆነ የውርርዱ ውጤት አስቀድሞ የታወቀ ከሆነ ወይም በአደራጁ አካል ተጽእኖ ውስጥ ከሆነ ወይም በስፖርት ዝግጅት፣ በደንበኛ ወይም በግለሰቦች ተጽእኖ ስር ከሆነ፡፡
- 3.6.4. አጠቃላይ ኦዶች/ግምቶች በትኬቱ የቀረበው 1፣00 ከሆነ መደቡ ሙሉ በሙሉ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- 4.1. ደንበኞች ከዚህ የውርርድ ጨዋታ ጋር ተያይዞ ማናቸውም ጥርጣሬ ካደረባቸው የውርርዱን እና የውድደድሩን ውጤት እንዲመረመርላቸው ጥያቄ የማቅረብ መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡ ነገር ግን የውርርዱንመንፈስ ካለማወቅ የተነሳ ወይም በትክክል በማለመለየት ምክንያት (ተመሳሳይ ስሞችን፣ አቋራጭ መንገዶችን ወዘተ በመጠቀም) የሚቀርቡ ቅሬታዎች ተቀባይበት አይኖራቸውም፡፡ በሌላ መንገድ በዚህ የውርርድ ህጎች እና ደንቦች ውስጥ ያልተካተቱ ማናቸውም የአሰራር ደንቦች አስመልክቶ ድርጅቱ የራሱን የመጨረሻ ውሳኔ የመስጠት በምቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ደንበኞችም በዚህ ውሳኔ ተገዢ የመሆን ግዴታ አለባቸው፡፡ ደንበኞች ለማንኛውም ቅሬታ እና የይገባኛል ጥያቄ በሙከተለው የኢሜይል አድራሻ፡ info@championbet.et ማቅረብ ይችላሉ፡፤
- 5.1. ደሰንበኞች የሚከተሉትን የውርረዱን ህጎች እና ደብኖች እንዲሁም ተያያዥ የስፖርት ውርርድ ህጎች እና ደንቦችን በመከተል ለህጉ ተገዢ መሆን ይገባቸዋል፡፡ በማንኘውም ምክንያት በአይነቱ ለየት ባለ ክስተት ወይም ዝግጅት ምክንያት የውርርድ ቦታ ወይም ቤት ከተዘጋ ደንበኞች ለሚያቀርቡት ማናቸውም ኪሳራ እና የጉዳት ካሳ ድርጅቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
| ገቢ የተደረገ | 100 ብር |
|---|---|
| ተ.እ.ታ 15% | 13.04 ብር |
| የተመዘገበ የጨዋታው ውርርድ | 86፣96 ብር |
| ከ1 ብር | እስከ 10,000.00 ብር (በ72 ሰአታት ውስጥ) |
|---|---|
| 10.001 ብር | እስከ 100,000.00 (በ7 ቀናት ውስጥ) |
| 100.001 ብር | እስከ 1,000,0000.00 (በ30 ቀናት ውስጥ) |
4. የይገባኛል ጥያቄዎች እና ቅሬታዎች
5. የማጠቃለያ ደንቦች